Global Association of Parishioners of EOTC
  • Home
  • About Us
  • Feedback
  • Contact Us
  • Donation
  • Links/Articles

እንኳን ደህና መጡ!

​

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ። አሜን!


“…ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ። ወንድሞቼ ሆይ፤ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎኤ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና። ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፣ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፣ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፣ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?….” ፩ኛ ቆሮ ፩፤፲-፲፬

በሐዋርያት ሥራ ም፰ ቁ፳፮-፴፱ እንደምናገኘው ኢትዮጵያውያን ክርስትናን መቀበል የጀመርነው ከሐዋርያት ዘመን ነው። ሃይማኖታችንም ጥንታዊትና ቀጥተኛ ናት።

አገራችን ኢትዮጵያን በነፃነቷ ካቆይዋት ሁኔታዎች አንደኛው ምክንያት ምእመናኑ ለቤተክርስቲያናቸው እና ለሃይማኖታቸው ያላቸው ታማኝነትና መሥዋዕትነት ነው። አሁንም ቤተክርስቲያናችን ስላጋጠሟት ችግሮች የሚቆሙላት ምእመናን አሏት።

በዓለም አቀፍ ደረጃ እና በኢትዮጵያም ቤተክርስቲያናችንን እና አገራችንን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እንዲወገዱ ብሎም ሰፊ ጥቅም እንዲገኝ የምእመናንን የጠነከረ ሕብረት የሚያስፈልጉ ብዙ ጉዳዮች እንዳሉ በመረዳት በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አባላት የግል ተነሳሽነት ይህ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ምእመናን ማኅበር ተቋቋመ።


Picture
Picture
Picture
የ3ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች
​
​
4ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች
Picture
Picture
Picture
Picture
Picture
Web Hosting by iPage